ተልዕኮ

        ተልዕኮ 

ሁሉ አቀፍና አዳዲስ የኮሙኒዩኒኬሽን መገናኛ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለህብረተሰቡ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማቶችን እንዲሁም የኢንቨስትመንት መረጃ

ራዕይ

  •     ራዕይ

  1. በ2022 ዓ.ም   በመ ረጃ የበለጸገ እና በሀገሩ ላይ መልካም ገጽታን የተጎናጸፈ ዜጋ ተፈጥሮ ማየት፣

ዓላማ

            ዝርዝር  ዓላማ  

1.ዜጎች በመንግሥት ቁልፍ አጃንዳዎች፣ የፖሊሲ አፈፃፀሞችና በወሳኝ ወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ጥራት ያለው መረጃን በወቅቱ እንዲያገኙ የተደራጀ የሚዲያና  ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መስጠት፣

2.በጠንካራ አደረጃጀትና አሠራር የተገነባ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን የመፈጸምና የማስፈጸም ዐቅም  መፍጠር፣

3. ትልልቅ ሀገራዊና ዞና   ባህላዊ ሁነቶች፣ የሚከበሩ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ በዓላት፣ በከፍተኛ አመራሮች የሚመሩ ጉብኝቶች)፣ ልዩ ልዩ ኢኒሼቲቮችን ማሳካት፣ እንዲሁም ሊከሰቱ የሚችሉ ቀውሶችን ማስተዳደር የሚችል የኮሙኒኬሽን ስርአት መፍጠር፣ 

4. የሚዲያ ሞኒተሪንግና የህዝብ አስተያት ጥናት በማካሄድ ውጤቱን ለሚመለከታቸው አካላት ለማቅረብ፣ 

5. ህዝብንና መንግስትን በማገናኘትና በማቀራረብ የዞኑን ገጽታ ለመገንባት፣

6. የመንግስት መረጃና ዲጂታል ሚዲያ ማስተዳደርና ማልማት፣

ዜና

በምስራቅ ጉራጌ ዞን "የውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት አቋራጭ መንገድ የለውም" በሚል መሪ ቃል የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።  

#ነሀሴ 20/2018(ቡታጅራ )  

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን "የውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት አቋራጭ መንገድ የለውም" በሚል መሪ ቃል የ2019 ዓ.ም የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት እቅድ ማስፈፀሚያ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።  

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊና ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ መሰረት ሽፋ እንደገለፁት ህገወጥ ስደት ለመከላከል የዉጪ ሀገር ስራ ስምሪት ዜጎች ወደ ውጪ ሀገር ስራ ፍለጋ ሲሄዱ ብቁ እንዲሆኑና በህጋዊ መንገድ ብቻ እንዲሄዱ በኢንሼቲቭ እየተሰራ መሆኑ ገልጸዋል ።