መንግስትልማትና ዲሞክራሲን ለማስፈን እና የሀገራችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ለማፋጠን ከተዘረጉ በርካታ ተቋማት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሴክተር በመንግስት የኢንፎርሜሽን ስርዓት ውስጥ ጉልህ ሚና በመጫወት በመንግስትና በህብረተሰቡ መካከል ቀልጣፋና ውጤታማ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር በማድረግ በዋና ዋና ዞናዊ፣ ክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሄራዊ መግባባት በመፍጠርና የሀገሪቱን በጎ ገፅታ በመገንባት ረገድ ጉልህ ሚና የመጫወት ተልዕኮን አንግቦ የሚንቀሳቀስ ተቋም ነው።የምስራቅጉራጌ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽንም ዞኑ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ የሚድያ አማራጮች በመጠቀም መረጃን ከመንግስት ወደ ህዝብ እና ከህዝብ ወደ መንግስት የማድረስ ስራው አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በተለይም የመንግስት የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ለህዝብ ተደራሽ ማድረግ፣ የህዝቦች አንድነት ማጠናከር፣ ገዢ ትርክት ማስረፅ፣ ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎች በፍጥነትና በጥራት ለህዝብ ተደራሽ የማድረጉን ስራ አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የመምሪያው ሚድያ ዘርፍምበመምሪያው የሚገኙ 3 ዋና ዋና ዳሮክቶሬቶች ማለትም የሚድያና ኮሙኒኬሽን፣ የመንግስት መረጃ ማዕከልና ዲጅታል ሚድያ አስተዳደር እና ሚድያ ሞኒተሪንግና የህዝብ አስተያየት ዳሬክቶሬቶችን የሚመራ ሲሆን የ3ቱም ዳሬክቶሬቶች ተግባር ተናበውና ተቀናጅተው ጥራት ያለውና ፈጣን መረጃ ለህዝብ ከማድረስ አንፃር ጉልህ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ሚድያ (ማህበራዊ፣የህትመትወይም የኤሌክትሮኒክስ) በሰው ልጅ የዕለት ተዕለት ህይወት ፣ስነ- ልቦና እና በሀገር ግንባታ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አላቸው። ሚድያ በአግባቡ ጥቅም ላይ ሲውል ለግልና ለሀገር እድገት ትልቅ አቅም አለው። በተቃራኒው ያለ ጥንቃቄ ጥቅም ላይ ሲውል በሰዎች መካከል ጥርጣሬን በማስፋት ግጭትና አለመረጋጋት ሊፈጥር ይችላል።ስለዚህ የተለያዩ የሚድያ አማራጮች የሀገራችን እድገትና ብልፅግና እንዲሁም የህዝቦች አንድነት በሚያጠናክር መልኩ በጥንቃቄ መጠቀም አለብን።