"ወጣቶች የሰላም አምባሳደር በመሆን ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለማጠናከር የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል" አቶ ታዬ ተስፋዬ
#ቡታጅራ | ጥር 15/2018 ዓ.ም
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታዬ ተስፋዬ ወጣቶች የሰላም አምባሳደር በመሆን ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ይበልጥ ለማጠናከር የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ገልፀዋል።
በዞኑ 3ኛው የምስራቅ ጉራጌ ዞን ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮናና የባህል ስፖርቶች ውድድር እየተካሄደ ሲሆን ውድድሩ መካሄድ ከጀመረ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል።
በትናንትናው ዕለት በመክፈቻ ፕሮግራም ላይ ከሰባቱም ወረዳና ከተማ አስተዳደር የመጡ የሰላም አምባሳደር ወጣቶች የዞኑ ህዝቦች ትስስር የሚያጠናክር ስጦታ ተለዋውጠዋል።
በዚህ ወቅት መምሪያ ኃላፊው አቶ ታዬ ባስተላለፉት መልዕክት ወጣቶች የህዝቦችን አንድነትና አብሮነት ይበልጥ ለማጠናከር ትልቅ ድርሻ እንዳለቸው ገልፀው በዚህ ውድድር ለመካፈል የመጡ ወጣቶች ያሳዩን አንደኛው ለሌላኛው መዋቅር ስጦታ የመለዋወጥና ፍፁም የወዳጅነትና አብሮነት ማሳያ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልፀው ለወጣቶቹ በመምሪያውና በስፓርቱ ቤተሰብ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።።
ኃላፊው አቶ ታዬ አክለውም እንዳሉት በውድድሩ ጅማሮ የታየው ስፖርታዊ ጨዋነት እስከ ፍፃሜው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።









