የመምሪያው አጠቃላይ ገፅታ
ይህ ተቋም ከ1985 አስከ 1987 ዓ.ም የማስታወቂያ መምሪያ፤ ከ1987 አስከ1990 ዓ.ም ባህልና ማስታወቂያ መምሪያ ከ1990 እስከ 1994 ዓ.ም ማስታወቂያ መምሪያ፣ ከ1994 እስከ 1996 ዓ.ም የማስታወቂያና ባህል መምሪያ፣ ከ1996 እስከ 2011 ዓ.ም ባህል ቱሪዝም የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ፣ ከየካቲት 2011 እስከ መስከረም 2012 ዓ.ም በአስተዳር ጽ/ቤት ህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት ከጥቅምት 2012 ዓ.ም ጀምሮ በአዋጅ ቁጥር 180/2012 መሰረት ከነሀሴ 2015 ዓ.ም ጀምሮ የምስራቅ ጉራጌ ዞን መንግስት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሆኖ እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡
የክልሉን አስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 180/2012 (እንደተሻሻለው) በአንቀጽ 9(3) መነሻነት ሴክተሩ በመምሪያ ደረጃ ተልዕኮውን በዋናነት ለማሳካት በሚያስችሉ ሦስት ዋና ዳይሬክቶሬትና በ3 ደጋፊ ዳይሬክቶሬት የተደራጀ ሲሆን እነዚህም፡-
የኮሚዩኒኬሽንና ሚዲያ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
የሚዲያ ሞኒተሪንግና የህዝብ አስተያየት ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬትር
የመንግስት መረጃ ማእከልና የዲጂታል ሚዲያ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
የልማት እቅድ በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ደጋፊ የስራ ሂደት
የሰው ኃብት አስተዳደር እና ልማት ደጋፊ የስራ ሂደት
የሰው ኃብት መረጃና ስታትስቲክ ደጋፊ ስራ ሂደት
የሰው ኃይል
ሴክተሩ ተልዕኮውን በአግባቡ ለመወጣት በሚያስችል መልኩ በጥናት በተለየው መሰረት እስከታችኛው መዋቅር በትምህርት ዝግጅትና የሥራ ልምድ ብቁ በሆነ የሰው ሀይል አየተደራጀ ሲሆን የሰው ሀይሉ ለቀጣይ የዕቅድ ዘመን አፈፃፀም ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡
በመምሪያው የሚሰጡ አገልግሎቶች፡-
- የልዩ ልዩ ህትመቶች ዝግጅትና ሥርጭት አገልግሎት፣
- ዜና፣ ፕሮግራም፣ ዶክመንተሪ፣ የአቋም መግለጫ አዘጋጅቶ የማስተላለፍና ተደራሽ የማድረግ አገልግሎት፣
- የመንግስት ፖሊሲዎችን፣ ፕሮግራሞችንና ዕቅዶችንና አፈጻጸሞችን የማስተዋወቅ አገልግሎት፣
- መንግስትን ከህዝብ የማገናኘነት አገልግሎት፣
- መንግስትን ከሚዲያ የማገናኘት አገልግሎት፣
- መረጃ የማከማቸት፣ የማደራጀት እና የማቅረብ አገልግሎት፣
- የተለያዩ መረጃዎችን የመልቀቅ አገልግሎት፣
- የክትትልና ድጋፍ አገልግሎት፣

Add new comment